top of page
Search

በአእምሮ ህመምተኞች ላይ ያለው መገለል እና መድሎ

  • Writer: Meron Simie
    Meron Simie
  • Jan 31, 2021
  • 2 min read

መገለል (Stigma)፡ ማለት አንድ ሰው ባለበዎት የአእምሮ ጤና እክል ምክንያት ሊያገኙ የተገባዎትን የማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ወይንም ሊገኙ በተገባዎት ቦታ ላይ እንዳይገኙ ሆን ተብሎ ገለል እንዲሉ ሲያደርገዎ፣ ቅድሚያ ሲነፍግዎት ወይን በአዎንታዊ ሁኔታ ሲያይዎት የሚፈጠር ስሜትና ሁኔታ ነው፡፡


መድሎ፡ (Discrimination) በአእምሮ ህመምዎ ምክንያት አንድ ሰው በአሉታዊ ሁኔታ ሲያስተነግድዎት፡፡


መገለል/ማግለል በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባል::


•በማኅረሰብ መገለል (public stigma): ሰዎች የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸውን ሰዎች እንዲፈሩ፣ ተቀባይነት እናዳያገኙና እንዲገለሉወይም እንዲገፉ የሚያነሳሳና በአእምሮ ህመም ላይ ማኅበረሰቡ ያለውን አሉታዊ ወይም አድሎአዊ እምነቶችና አመለካከቶችን ውቅር ነው፡፡


•ራስን ማግለል (Self stigma): የአእምሮ ጤና መታወክ ችግር ያለባቸው ሰዎች በማኅበረሰቡ የሚደረስባቸውን መገለል ወደ እራሳቸው በመውሰድ ሰዎች ስለ እነሱ የሚናገሩትን አሉታዊ ነገሮች በማመን እንዲሁም በመቀበል አራሳቸውን እንዲያገሉና ከሰው እንዲደብቁያ ደረጋል ፡፡


•ተቋማዊ መገለል (institutional stigma):በሥራ፣ በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ተቋማት ውስጥ በማወቅም ሆነ ወይም ባለማወቅ የአእምሮ ጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች ዕድሎችን የሚከለክሉ አሰራሮች፣ድርጅታዊ መዋቅሮችና ፖሊሲዎችን የሚያካትት ስልት ነው ፡፡

በሀገራችን እንደ ዋና ምሳሌነት የሚወሰደው በመንግስትም ሆነ በግል የጤና ተቋማት በኩል የሚስተዋለው ለአእምሮ ጤና እንክብካቤ የሚሰጠው ዝቅተኛ ትኩረትና ድጋፍ ከሌሎች የጤና እንክብካቤ ፕሮግራምና እቅዶች ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ ያነሰ መሆኑ ነው፡፡


አብዛኛው ጊዜ የአእምሮ ጤና መታወክ ችግር የሚያጋጥሟቸው ሰዎች ተገቢውን ህክምና ድጋፍና ክትትል በወቅቱ ካገኙና ከተከታተሉ ሙሉ በሙሉ ይድናሉ ፣ አሊያም ደግሞ ከህመሙ ጋር አስፈላጊውን የህክምና የመድሀኒት ክትትሎችን በማድረግ አብረው መኖር እና ማስተዳደር ይችላሉ፡፡

የአእምሮ ጤና ችግር እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራትማኅበረሰብ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ የተረሳ፣ ትኩረት የተነፈገረውና የተሳሳተ ግንዛቤ ያለው ነው፡፡

የአእምሮጤና ችግር ከማኅበረሰብ ጤና ውስጥ እንደሌሎቹ የጤና እክሎች ሁሉ ትኩረት ሊሰጠው የገባል፡፡


በሀገራችን እንደ የጤና እክል የማየታየው የድብርት(ድባቴ) በዓለም ዙሪያ ዋነኛው የአእምሮ ጤና ዋነኛ ችግር ነው ፣ ከዚያም በመቀጠል የአእምሮ ጭንቀት ፣

ስኪዞፈሪንያ እና ባይፖላር ዲስኦርደር

(Schizophrenia and bipolar disorder) ተብለውየሚጠሩት ይካተቱበታል ::


የአእምሮ ጤና መታወክ ከሚያስከትላቸው ዘርፍ ብዙ ችግሮች መሀከል ማህበራዊ መገለል አንዱ ሲሆን የሚያሳድረውም ተጽእኖ ቀላል አይደለም፡፡

ማኅበራዊ መገለል ከሚያደርሳቸው ዋና ዋና ተፅኖች ውስጥ ፣

•ቅድሚያ መከልከል፣

•ትኩረት መነፈግ፣

•ተገቢውን አገልግሎ አለማግኘት ሲሆኑ፤

ስራ አጥነት እና ድህነት ከአእምሮ ህመም ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው ስለዚህ መገለል እና አድልዎ ሰዎችን በህመሙ ዑደት ውስጥ ሊያጠምዳቸው ይችላል::


ምንም እንኳን ብዙ የአእምሮ ህመም ተጠቂው ህዝብ እየጨመረ ቢሆንም፣ ከግንዛቤ እጥረት ጋር በተያያዘ ከአእምሮ ህመም ጋር ጠንካራ የማህበራዊ መገለል አለ፣ እናም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በሁሉም የሕይወታቸው ዘርፎች አድልዎና መገለልሲ ያጋጥማቸው ይታያል፡፡


የአእምሮ ህመም ካጋጠማቸው አስር ሰዎች መካከል ዘጠኙ መገለልና መድልዎ በሕይወታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራልተብሎ ይታመናል ፡፡


ማንኛውም የአእምሮ ጤንነት ችግር ያለባቸውሰዎች ፣ የረጅም ጊዜ የጤና ችግር ሁኔታ ካጋጠማቸው ወይም የአካል ጉዳት ካለባቸው ማህበረሰብ ክፍሎች ወስጥ እንደሚመደብ ይታውቃል::


በዚህንም ምክንያት

•ቋሚ ስራ ማግኘት ፣

•በተረጋጋ እና በረጅም ጊዜ የፍቅር/ጎደኝነት ግንኙነት ውስጥ መቆየት ፣

•በተረጋጋ ቤት ውስጥ መኖር ፣በህብረተሰቡ ውስጥ በሰርክ የማህበራዊ ጉዳዮች ተካፋይ መሆን ፣ እና የመሳሰሉትን ማህበራዊ እና ሰብዓዊ የኑሮ ሁኔታዎች በቀላሉ

ማከናወን ይከብዳቸዋል ተብሎ ይታመንናል::


ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት ማህበረሰቡ ስለ የአእምሮ ህመም እና በሰዎች ላይ እንዴትተጽዕኖ እንደሚያሳድር የተሳሳተ አመለካከት ስላለው እና በዘርፉ ያለው ግንዛቤ በጣም የመነመነ በመሆኑም አብዛኛው ሰው እንደምንመለከተው የአእምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች ጠበኞች እና አደገኛ ናቸው ብሎ ያምናል ፣ እውነታው ግን የአእምሮ ህመምተኞች በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት ከማድረስ ይልቅ እራሳቸው የጥቃት ሰለባዎች ሲሆኑ እራሳቸውን ለመጉዳት አደጋ የተጋለጡናቸው፡፡


የአእምሮ ጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች መገለልእና መድልዎ የአእምሮ ጤንነትን ያባብሳሉ ተብሎ ይታመናል ፣ ከዚህም በተጨማሪ እርዳታ የመጠየቅ እድላቸውን እና ህክምናውን በአግባቡ ለመከታተል እንቅፋትስለሚሆንባቸው በፍጥነት ህክምናቸውን ተከታትለው ማገገሙን ሊያዘገየው ወይምሊያደናቅፉ ይችላሉ፡፡


በኢትዮጵያ ውስጥ ለአእምሮ ጤና ህመም በተቌማት ውስጥ ከተነፈገው ትኩረት የተነሳ የማኅበረሰቡ ንቃተ ህሊናና ለአእምሮ ጤና ያለው ግንዛቤ ውስን መሆን የተነሳ የአእምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ባህሪያቸው ቁጡና ተደባዳቢ ናቸው ተብሎ ስለሚገመት ጭፍን ጥላቻን ያስተናግዳሉ::





ree

 
 
 

Recent Posts

See All
Expressing Love.

As a community we have a lot to work on how to express our love for others. Most of us though we were raised in a loving and supportive...

 
 
 

Comments


Post: Blog2_Post

Subscribe Form

Thanks for submitting!

  • Twitter

©2021 by ስለኛ-AboutUs. Proudly created with Wix.com

bottom of page